የ Burien ከተማ ብዙ ሰዎችን ከሲቪክ እቅድ ሂደቶች ጋር ለማገናኘት ከ Burien ልዩ ልዩ ማህበረሰቦች ከታመኑ መሪዎች ጋር በመተባበር የ Burien የማህበረሰብ አደራጆች ፕሮግራምን እየጀመረ ነው። ፕሮግራሙ የተመሰረተው በታማኝ ተሟጋች ሞዴል ላይ ሲሆን፣ ይህም እንደ ባለሙያዎች ማህበረሰባቸው እንዲበለጽግ በሚፈልጉት ላይ መጤ እና ስደተኛ ማህበረሰቦችን ጨምሮ፣ ከተለያዩ የባህል፣ የጎሳ እና የዘር ማንነቶች እና ልምዶች የተገኙ የመሪዎችን ችሎታ እና እውቀት የሚያከብር ነው።
የ Community Connectors የከተማውን ሰራተኞች በወቅታዊ የተሳትፎ ልምምዶች ላይ ምክር ይሰጣሉ እንዲሁም ከተማው ማህበረሰቡን በፓርኮች፣ በመዝናኛ እና በክፍት ቦታ ፕላን፣ አጠቃላይ እቅድ እና የትራንስፖርት ማስተር ፕላን በማዘመን ላይ እንዲያሳትፉ ያግዛሉ። እንዲሁም የማህበረሰብ አስተያያት ምልልሶችን ለማሻሻል ከከተማ መምሪያዎች ጋር አብረው ይሰራሉ።
የፕሮግራሙ የመጀመሪያ ምዕራፍ ስፓኒኛ፣ ቬትናምኛ ወይም አማርኛ አቀላጥፈው የሚናገሩ አድራጆችን በመመልመል ላይ ያተኩራል። የሚከተሉትን ለማድረግ ከከተማው ሰራተኞች ጋር አብረው ይሰራሉ፦
- በተሳትፎ፣ በአገልግሎት አሰጣጥ እቅዶች እና በፕሮግራም ልማት ላይ ምክር ለመስጠት
- ከብሄረሰብ ሚዲያ እና ከሌሎች የማህበረሰብ ሚዲያዎች ጋር ለመስራት
- ከነዋሪዎች እና ከንግዶች ጋር ለመሳተፍ
- ሰነዶችን ለመተርጎም እና በዝግጅቶች ላይ ለማስተርጎም
- የማህበረሰብ አባላትን ከሌሎች አገልግሎቶች እና የመረጃ ምንጮች ጋር ለማገናኘት
የ Burien Community Connectors በሰዓት $50 ካሳ ይከፈላቸዋል እና በ Burien መኖር፣ መስራት ወይም ማምለክ አለባቸው፣ አለበለዚያ ከከተማው ጋር እኩል የሆነ ጠንካራ ግንኙነት ማሳየት አለባቸው።
እንዴት ማመልከት እንደሚቻልን ጨምሮ ስለ ፕሮግራሙ በ burienwa.gov/connectors የበለጠ ይወቁ.